መነሻ ዝግጅቶች የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።
መጪ workshop

የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።

የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።

ስለ ዝግጅቱ

የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ። ከከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የድጋፍና የክትትል ቡድን የድሬደዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ላይ ምልከታ አካሂዷል። ምልከታው በመሬትና መሬት ነክ መረጃ ስራዎች፤ የመሬት ልማትና አስተዳደር ስራዎች እንዲሁም የቅየሳና የጂኦስፓሻል ስራዎች በተጨማሪም የልማት ተነሺዎችና መልሶ ማቋቋም ላይ ትኩረቱን አድርጓል። ለድጋፋዊ ክትትል ቡድኑ የቢሮው የአምስት አመት አፈጻጸምን በንጽጽር እና የ2018 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፓርት በቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ዘላለም ወጋየሁ ቀርቧል። የድጋፋዊ ክትትል ቡድኑ አባላትም የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን የተከናወኑ ተግባራት የሚበረታቱ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን የመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ እንዲሁም ከመብት ፈጠራ ጋር በተያያዘ የተከናወኑ ተግባራት የተሻሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በማጠቃለያውም ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ ሁሴን ጌዲ እንደተናገሩት ቢሮው በየጊዜው አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝና ይህንኑ ዘመናዊ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል።

የፎቶ ማዕከል

የፎቶ ማዕከል

የዝግጅት ዝርዝሮች

  • Friday, May 1, 2026
    08:30 AM – 07:08 AM
  • የሚጠናቀቅበት
    May 29, 2026
  • Diredawa
  • አዘጋጅ
    land Management
ወደ ዝግጅቶች ተመለስ